መለያዎ

የMezgeb መለያዎን ይሰርዙ

የMezgeb መለያዎን በመተግበሪያው ውስጥ ራስዎ መሰረዝ ይችላሉ። መተግበሪያው ከሌለዎት ወይም መግባት ካልቻሉ ይጠይቁን፤ እኛ እንሰርዝልዎታለን።

በመተግበሪያው ውስጥ

  1. Mezgebን ይክፈቱና ይግቡ።
  2. «ተጨማሪ»ን፣ ከዚያም «የግል መረጃ እና የይለፍ ቃል»ን ይንኩ።
  3. «መለያ መሰረዝ» በሚለው ስር «መለያውን ሰርዝ»ን ይንኩ።
  4. የይለፍ ቃልዎን ያስገቡና «መለያውን ሰርዝ»ን ይንኩ።

በስልክዎ ላይ ገና ያልተላኩ ሽያጮች ካሉ፣ መተግበሪያው መጀመሪያ ከኢንተርኔት ጋር ተገናኝተው እንዲላኩ እንዲፈቅዱ ይጠይቅዎታል።

ያለ መተግበሪያው

የሚገቡበትን ስልክ ቁጥር ጽፈው መለያው እንዲሰረዝ መልዕክት ይላኩልን። ጥያቄው ከእርስዎ መሆኑን ለማረጋገጥ ከዚያው ቁጥር እንዲያረጋግጡ ልንጠይቅዎት እንችላለን። ሲጠናቀቅ እናሳውቅዎታለን።

ምን ይሆናል

  • መለያዎ ይሰረዛል። ከሁሉም ስልኮች ይወጣሉ፤ በዚያ መለያ ዳግም መግባት አይችሉም።
  • ባለቤት ከሆኑ ድርጅትዎም ይሰረዛል፦ በድርጅቱ ያሉት ሁሉ ይወጣሉ፤ መግባትም አይችሉም።
  • ወደ ስልኮችዎ የሚላኩ ማሳወቂያዎች ይቆማሉ።
  • ስልክ ቁጥሩን አዲስ መለያ ለመክፈት መጠቀም አይቻልም። ቁጥሩን ዳግም ከፈለጉ ያግኙን።
  • ለአንድ ሱቅ የሚሠሩ ከሆነ፣ ያደረጓቸው ሽያጮችና ሌሎች መዝገቦች የሱቁ ስለሆኑ ከሱቁ ጋር ይቆያሉ።

የምናስቀምጠው

እንደ ክፍያ ያሉ አንዳንድ መዝገቦች ለሂሳብ አያያዝ መቀመጥ ሊኖርባቸው ይችላል።

የግላዊነት ፖሊሲውን ያንብቡ